የ2017/ 2025 /መጋቢት የመድኃኔዓለም (ጥንተ ሥቅለቱ ) የሚታሰብበት በዓል በደማቅ ሁኔታ ተከብሯል ።
የጌታችን የመድኃኒታችን የመድኃኔ ዓለም ጥንተ ስቅለቱ በሚታሰብበት በመጋቢት ወር የመድኃኔ ዓለም ዓመታዊ ክብረ በዓል መጋቢት 27 እና 28 2017 በፈረንሣይ ማርሴይ ከተማ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን በደማቅ ሁኔታ ተከብሮ ዋለ|።
የጣሊያን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ በተገኙበት ከፈረንሣይ እና ከቤጅየም እካባቢ ያሉ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ፣የአድባራት አስተዳዳሪዎች፣ዲያቆናት፥መምህራን፣ የየአድባራቱ የሰንበት ተማሪዎች ፣ምዕመናን እና ምዕመናት በተገኙበት ከዋዜማው መጋቢት 27.2017 (April 5/ 2025) ጀምሮ እጅግ ደስ በሚያሰኝ ሁኔታ ዓመታዊ በዓሉ ተከብሯል|።
ከዋዜማው ጀምሮ ሌሊቱን ሙሉ በምስጋና ሊቃውንቱ እንዲህ በማለት ዚቅ በእንተ ማርያም ወላዲትከ፣ወበእንተ ዮሐንስ መጥምቅከ፣ወበእንተ ኩሎሙ ቅዱሳኒከ ርድአነ ወትረ በኃይለ መስቀልከ፣ ኢታስተኃፍረነ እግዚኦ በቅድሜከ
በማለት ሲያወድሱ አድረዋል በጠዋቱ መርሐ ግብርም በቆሞስ መልአከ ሕይወት አባ ዐጋ ዘአብ እየተመራ ሥርዓተ ቅዳሴው ከተጠናቀቀ ቦኃላ ከየአድባራቱ የመጡ የሰንበት ተማሪዎችና የደብሩ ሰንበት ት/ቤት መዘምራን በህብረት በመሆን ያሬዳዊ ዝማሬን አቅርበዋል።
በመቀጠል ዲ/መስፍን ኃይሌ የጣሊያን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ እለቱን በማስመልከት ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ አስደናቂው ድል ያለውን በመጥቀስ በጥሩ ሁኔታ በማብራራት ትምህርት አስተምረዋል ።
የጣሊያን እና አካባቢው ሀገረ ስብከት ዋና ጸሐፊ ዲ/ን መስፍን
ዲ/ን መስፍን ከትምህርታቸው ባሻገር በዚህ ደብር የነበረው ችግር ሁሉ ተቀርፎ እንደዚህ በአንድነት በመሆን ይህንን ታላቅ በዓል በጋራ ሲከበር በማየታችው በደስታ ስሜት የገለጹ ሲሆን የሀገረ ስብከታችን ሊቀ ጳጳስ ብጹዕ አቡነ ሕርያቆስ በተደራራቢ ሥራ ምክንያት በዛሬው ዕለት ባይገኙም በሚቀጥለው ጊዜ እንደሚመጡና የተሰማቸውን የደስታ ስሜትና ስለ በዓሉ አከባበር መልእክት እንደሚያስተላልፉ ገልጸለዋል ።
በተለያየ ምክኒያት ክርስቲያኖች ከሀገር ወጥተው በስደት ቢቆዩም የቤተ ክርስቲያን ፍቅር በልባቸው ጽላት ላይ የተጻፈ ስለሆነ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥም ቢያልፉም ባገኙት አጋጣሚ ከርስትናቸውን በአደባባይ ይመሰክራሉ ለዚህ ምሳሌ የሚሆነው በማርሴይ መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን
አቶ ፋሲል ጥበቡና ባለቤታቸው ወ/ሮ ሠናይት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን የክርስቶስ አምላክነት የሚሰበክባት ፣ በጠበልና እምነት ከሕመም ፣መዳን የሚቻልባት እውነተኛ ሃይማኖት እንደኾነች አምናለው፣ ይሁን እንጂ ሀገራችን ለቀን በስደት ሀገር ኑሮ መስርተን ስንኖእ ሦስት ልጅችን አርፍተናል ነገር ግን በልዩ ልዮ ምክንያት ልጆቻችንን የሥላሴን ልጅነት ሳያገኙ ለአቅመ አዳምና ለአቅመ ሄዋን ደርሰው ነበር ፈረንሣይ ሀገር ከመጣን ቦሃላ እግዚአብሔር ፈቅዶ የንስሓ አባት ይዘን ልጆቻችንም መሠረታዊ የሃይማኖት ትምህርት እንዲማሩ አድርገን እነሆ በዛሬዋ ዕለት እኔና ባለቤቴ ንስሓ ገብተን ሥጋና ደሙን ለመቀበል ስንበቃ ልጆቻችንም የሥላሴን ልጅነት በዛሬዋ ዕለት አግኝተዋል በማለት የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።
በተጨማሪም ዲ/መስፍን ለቤተክርስቲያኑ የሚውል የገቢ ማሰባሰቢያ ቅስቀሳ አድርገው እጅግ አስደናቂ ሥራ ሰርተዋል። ምዕመናንም ደስ እያላቸው ያላቸው እርዳታ ለግሰዋል ።
በዕለቱ የተገኙ አባቶች የተለያየ መልክቶችን አስተላልፈዋል ምክር ሰጥተዋል አበረታተዋል
መልአከ ሕይወት ቆሞስ አባ ጋዘአብ ፣ መልአከ ሰላም ቀሲስ ሰሎሞን ኃይሌ፣ ቀሲስ ጋሻው ቅኔ አዋቂው ዲ/ ፅጹብ
የደብሩ አስተዳዳሪ መምህር ቀሲስ ተስፋ ሥላሴ ሊቃውንቱን እና ምዕመናኑን በማመስገን በፈረንሣይ የካህናት ህብረት ጠንክሮ መሥራት እንዳለበትና ወደፊትም ብዙ ሥራዎች ይጠብቁናል በተለይ እንደማርሴይ እና አከባቢው ብዙ የተጀመሩ የሰላምና የማቀራረብ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው ሁሉም ሰው ስለ ሰላም የማስተማር ኃላፊነት አለበት በማለት መልእክት አስተላልፈዋል።
የማርሴይ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ መምህር ቀሲስ ተስፋ ሥላሴ
የማርሴይ ደብረ መድኃኒት መድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን ዋና አስተዳዳሪ መምህር ቀሲስ ተስፋ ሥላሴ ታቦተ ህጉ ከመንበሩ ወርዶ ህዝቡን ከባረከ ቦኃላ በሰንበት ት/ቤት መዘምራንና በሊቃውንቱ ወረብ እየታጀበ ወደ መንበረ ክብሩ ተመልሷል ከምሽቱ ጀምሮ የተጀመረው ክብረ በዓል ከቀኑ 12:15 ላይ በሰላም ተጠናቋል እንግዶችም የተዘጋጀውን ጸበል ጻድቅ እየቀመሱ ተመልሰዋል።
በነገር ሁሉ የረዳን የአባቶቻችን አምላክ እግዚአብሔር ይክበር ይመስገን ረድኤተ እግዚአብሔር አይለየን
ታቦተ ህጉ በሊቃውንተ ቤተክርስቲያን በሰንበት ት/ቤቶች መዘምራን እና በምዕመናን ታጅቦ
የጽሑፍ አስተያየቶች